top of page

በኢትዮጵያ በመካከለኛው ዘመን በተደረገ የስርወ-መንግስት ለውጥ ሁለገብ ጥናትና የአርኪኦሎጂ ምርምር

ስለ እኛ

ይህ ዘርፈ ብዙ የጥናት መስክ በተለይም የአርኪኦሎጂ ፕሮጀክት በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የላሊበላን አካባቢ (ላስታን) ስለ ተቆጣጠሩት የአማራ ህዝቦች ያለንን እውቀት የበለጠ ለማሳደግ ይፈልጋል፡፡

እኛ የአካባቢውን ማህበረሰብ ባህሉን ለመረዳትና ለማወቅ ፍላጎት አለን፡፡ ፕሮጀክቱ ስነ-ህይወታዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ቁሳዊ ትርጉምን በማብራራት በአገው ቋንቋ ተናጋሪዎችና ወደ አካባቢው በመጡት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል የተደረጉትን የግንኙነት ውጤቶች የማብራራት አላማ አለው፡፡ 

ለዚህም ቁልፍ መለኪያዎችን በመመልከት ጥናት በምናደርግባቸው መዳረሻዎች (sites) የንጽጽር መረጃ ቋትን እየገነባን ነው፡፡ እነዚህም የመልክዓ-ምድር አጠቃቀም፣ ስነ-ህንጻ፣ የሸክላና ባህላዊ ቁሶች፣ የብረት ውጤቶች፣ የግድግዳ ስዕሎችና ሌሎች ልዩ ልዩ አይነት ገጽታዎች ያላቸው እንደ ዋሻ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ግድግዳዎችን ያስጌጡ የዝቅተኛ እርከኖች ቅርጾች ተስተውለዋል፡፡ ጎን ለጎንም  የሚስተዋሉት የመካከለኛው ዘመን የግድግዳ ላይ ስዕሎችም በግልጽ ከንጉስ ይኩኖ አምላክ ጋር የተዛመዱ ናቸው

Introducing SolZag Project
Play Video

ሰኔ 6/2012 ዓ.ም በዲግኔሽን በዓል ላይ ይህንን ቪዲዮ አርሞ ላስተላለፈልን ለዲግቬንቸርስ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

Genete Mariyam monolithic  1.jpg

አርኪኦሎጂ

dsc_0673.jpg

ሥነ-ጥበባዊ ታሪክ

_dsc1891.jpg

ተደራሽነት

የፕሮጀክቱ መዳረሻዎች

የፕሮጀክቱ መዳረሻዎች

የመልዕክት ዝርዝራችንን ይቀላቀሉ

የፕሮጀክቱ አዳዲስ ዜናዎችን ለመቀበል

Thanks for subcribing!

bottom of page