top of page
2_DSC1198 Gännätä Maryam.JPG

ተደራሽነት 

ጥናታችንን በምንሰራበት አካባቢ ለሚኖሩ ማሀበረሰቦች ፕሮጀክቱ ተጨማሪ እሴት የሚያመጣ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁልጊዜ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ይህም በቁፋሮ እርዳታ ላደረጉ የአካባቢው ወጣቶች ጊዚያዊ የስራ ዕድል መፍጠርና ለአርኪኦሎጂ ተማሪዎችና ለወጣት ባለሙያዎች ስልጠና መስጠትን ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም የቡድኑ አባላት በአዲስ አበባ፣ በመቀሌና በወልዲያ ዩንቨርሲቲዎች ንግግርና ገለጻ እንዲያደርጉ ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡ 


ከዚህ በፊት የተሰሩ የተደራሽነት ስራዎችን ለአብነት ያህል ብንጠቅስ ፕሮጀክቱ በደርዘን የሚቆጠሩ የመማሪያ መጽሐፍትንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመግዛት ለገነተ ማርያም የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ድጋፍ አድርጓል፡፡ 


ለምርምር ግኝቶቻችን ማስቀመጫ የሚሆን ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ለሰጠን ለላሊበላ የባህል ማዕከል ፕሮጀክቱ ማዕከሉ ያለበትን ጉድለት ለመሸፈን የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ መደበኛ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓል፡፡


በ2001 ዓ.ም ፕሮጀክቱ ስራ ሲጀምር የእኛ ስራ ለአካባቢው ማህበረሰብ በምን አይነት መንገድ ሊጠቅማቸው እንደሚችልና ልንረዳቸው የምንችለው ልዩ ፍላጎቶቻቸው ምን እንደሆኑ ለመለየት ከሃይማኖት አባቶችና ከምዕመናን ጋር ተወያይተናል፡፡


አንዱ ጥያቂያቸው የነበረው ወደ ላሊበላ ከሚሄዱ የውጭ ጎብኝዎች መካከል የገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን በጣም ጥቂቶቹን ብቻ የሚያስተናግድ ስለሆነ ተጨማሪ ጎብኝዎችን ለመሳብና ወደ ቦታው እንዲሄዱ ለማስቻል ቤተክርስቲያኑን በማስተዋወቅ እንድንደግፋቸው ነበር፡፡ ሌላኛው ጥያቂያቸው ደግሞ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሚገኝ የንጉስ ይኩኖ አምላክን የህይወት ታሪክ የያዘ በግዕዝ የተጻፈ የብራና መጽሐፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ እንዲተረጎምና እንዲታተም የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግላቸው ጠይቀውናል፡፡ የትርጉም ስራው የተጀመረው በ2002 ዓ.ም የነበረ ቢሆንም በስራው ውስብስብነት ምክንያት ከታቀደው በላይ ረዘም ያለ ጊዜ ፈጅቶ መጽሐፉ በ2011 ዓ.ም ታትሟል፡፡ እኛም ቤተክርስቲያኗ ለጎብኝዎች ሽያጭ የምታቀርበው የመጽሐፉን 1000 (አንድ ሺህ) ቅጅዎች እንዲታተሙ የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ አድርገናል፡፡ አሁን ላይ ለውጭ ቱሪስቶች በሽያጭ ሊቀርብ የሚችል የመጽሐፉን የእንግሊዘኛውን ትርጉም እያዘጋጀን እንገኛለን፡፡  

bottom of page