top of page
3-Emekina Medhani Alem-39 (cropped).jpg

የስነ-ጥበብ ታሪክ

ከዛጔ ሥርወ-መንግስት ወደ ሰሎሞናዊው ስርወ-መንግስት የነበረው ሽግግር አንዳንድ ሰዎች በተለይ ከንጉስ ይኩኖ አምላክ ጋር በተዛመደ በልዩ ዘይቤ /style/ የቤተክርስቲያኖቻቸው ግድግዳዎች ላይ ስዕል እንዲስሉና በምስል በመግለጽ የእጅ ጹሁፎችን እንዲጽፉ (ሥነ-ጥበብን ማሳድግ) ያበረታታ ይመስላል፡፡ ከአዲሱ ገዥ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተመሳሳይና ተከታታይነት ያላቸው የግድግዳ ስዕሎች በከተማዋ ዙሪያ ባሉ ገነተ ማርያም፣ ብልባላ ቂርቆስና እመኪና መድሃኒዓለም አብያተክርስቲያናት ውስጥ ተስለዋል፡፡ በአንጻሩ የዛጔ ነገስታት በአጠቃላይ በኪነ-ህንጻ ጥበባቸው የበለጠ ይታወሳሉ፡፡


ከንጉስ ይኩኖ አምላክ ጋር ግንኙነት ያላቸው የግድግዳ ስዕሎች ከዛጔ ስርወ-መንግስት ጋር ከሚዛመዱ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ከሚገኙ የግድዳ ስዕሎች ጋር በአሳሳል ዘይቤያቸው በፍጹም የተለዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በዛጔ ስርወ-መንግስት የስልጣን ዘመን በተሰራው ይምርሓነ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ስዕሎች በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተሰሩ የግብጽ ኮፕቲክ ገዳማት የግድግዳ ስዕሎች ጋር በጣም ይመሳሰላሉ፡፡ 


በአንጻሩ የአማራ ሥዕሎች ምንም እንኳን በግልጽ በዚያው/በተመሳሳይ ዘመን ከተሰሩ በአረብ ክርስቲያናዊ ስዕሎች የተቃኙ ቢሆኑም በዋናነት በአካባቢው የእጅ ስራ የተሰሩ ናቸው፡፡ የዚህ ከውጭ የመጣ ምስልን/ስዕልን መቀበልና እንደገና መተርጎም ስለ አካባቢው ሁኔታዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን አየጨመረ ነው፡፡ በተጨማሪም ብዙውን ጊዜ ከአካባቢው በተለይም ከእንስሳት የሚመጡ (የእንስሳት ውጤቶችን) አስፈላጊ ነገሮችን ያካትታሉ (የእስሳት ቅሪተ አካልን ተመልከት) ፡፡


ከፕሮጀክቱ አላማዎች አንዱ ሁሉንም ስዕሎች ከቅርጻቸው፣ ስዕላዊ መግለጫቸውን፣ ቀለማቸውን፣ ግልጋሎት ላይ የዋሉ መከወኛዎችንና የተመረቱበት ጊዜ መቼ ሊሆን ይችላል የሚለውን መገምገም ነው፡፡ በወቅቱ አዲሶቹ ገዥዎች የአረበኛ ክርስቲያናዊ ጽሑፎችን ስልታዊ በሆነ መንገድ ወደ ግዕዝ እንዲተረጉሙና በዋናነት የቀድሞ መሪዎቻቸው የሆኑትን የዛጔ ነገስታት የህይወት ታሪክና ዜና መዋዕልን ያካተተ ትልቅ የሥነ-ጹሁፍ አካል እንዲፈጠር ያበረታቱ ነበር፡፡ በተለምዶ ከይኩኖ አምላክ ጋር የተቆራኘው የደብረ ሃይቅ እስጢፋኖስ ገዳም በዚህ አዲስ አጽንኦት/ትኩረት ባለው ስዕልና ጹህፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ የክርስቲያን የግድግዳ ስዕሎች አካላዊ ውህደትና በዋሻ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ግድግዳ ላይ በግልጽ የሚታዩት የቅድመ-ክርስትና የአደንና የእረኝነት ትእይንቶች አስደናቂ ናቸው፡፡

እንዲሁም በንጉሳዊ ዜና መዋዕሎች እንደተረጋገጠው የክርስትና ሃይማኖት በመከካለኛው ዘመን በሁሉም አካባቢ ተቀባይነቱ እየጨመረ መምጣቱና ስራ ላይ መዋሉን ከግምት ውስጥ በማስገባት እየተመረመረ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሁለት ተቀናቃኝ ስርወ-መንግስታት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ህንጻዎች መካከል ሊኖሩ የሚችሉ ግንኙነቶችን በተለይም በዋሻ ሚካኤል አካባቢ የተገኘው የዋሻ ጥበብ እና የአክሱማውያን ቅርስ ያሉባቸው መልክዓ-ምድሮች እየተጠኑ ይገኛሉ፡፡

 

bottom of page