top of page
4- _DSC1577.JPG

ጥበቃ

ባለፉት አመታት እኛ እየሰራንባቸው ያሉ ቅርሶች ስጋት እንደተደቀነባቸው የበለጠ እየተገነዘብን መጥተናል፡፡ ከገነተ ማርያም ቤተክርስትያን ግቢ ውጭ የሚገኙት ቀብሮች ሁኔታ የስጋታችን ምክንያት ናቸው፡፡ ቀብሮቹ በ2005 ዓ.ም እንደገና በተገኙበት ጊዜ ቀደም ብሎ መረጋገጥና የግንባታ ስራዎች መጀመር በዋናነት የጉዳት መንስኤዎቻቸው ነበሩ፡፡ ብዙውን ጊዜ የአካባቢው ማህበረሰብ ቦታውን እየተጠቀመ የመቀጠል ፍላጎት አለው፡፡ እናም በ2007 ዓ.ም መቆፈርና ማስወገድ ያልቻልነው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቀብሮቹ እጣፈንታ በህብረተሰቡና በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባስልጣን የመደራደርያ ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡


በተጨማሪም በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ያሉትን የግድግዳ ስዕሎች ያሉበትን ሁኔታ እየተከታተልን እንገኛለን፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ የግድግዳ ስዕሎች በብዙ ጉዳዮች ላይ የተረጋጉ ሆነው ቢታዩም ብዛት ያላቸው ስጋቶች አሏቸው፡፡ እነዚህም ሊከሰት የሚችል የአለት መውደቅ፣ መቀርፈት/መላጥ፣ በሻማ/በጧፍ ጭስ መጎዳትና የእርጥበት ሰርጎ መግባት ናቸው፡፡ የእርጥበት ሰርጎ መግባት በተለይ በዋሻ ውስጥ አብያተክርስቲያናት ላይ ይታያል፡፡ ነገር ግን ፍልፍል አብያተ-ክርስቲያናት የሆኑት ገነተ ማርያምና ብልባላ ቂርቆስ የመከላከያ ጣሪያ ያላቸው ቢሆንም እርጥበት ሰርጎ ይገባባቸዋል፡፡ ሌሎች ከባድ መበላሸቶችም ሳይታወቁ አምልጠው ይሆናል፡፡


ስለሆነም የስዕሎቹን ጥንካሬ ለመገምገም ከስዕል እንክብካቤ ባለሙያ ከሆኑት ስቴፈን ሪከርብይና ሊሳ ሸከደ ጋር በመሆን የእንክብካቤ የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ እየተዘጋጀን ነው፡፡ በተጨማሪም በስዕሎቹ ላይ አጥፊ የሆኑ ዘዴዎችን መጠቀምን በማስወገድ ማንኛውንም የመበላሸት መንስኤ ዋና ዋናዎቹን ምክንያቶች ተመልክቶ ማቅረብ ነው፡፡ የመጀመርያውን የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ 2012 ዓ.ም ታቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን የኮሮና (COVID-19) ወረርሽኝ በቁጥጥር እስኪውል ድረስ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡

 

bottom of page