top of page

የፕሮጀክቱ ኃላፊ

ዶ/ር ታንያ ትራይብ በለንደን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት ማዕከል/Centre of African Studies, SOAS University of London. በአፍሪካ ስነ-ጥበብና በአርኪኦሎጂ የትምህርት መስኮች በማስተማርና በመመራመር ለ25 ዓመታት ያህል አገልግላለች፡፡ 


በአሁን ጊዜ ጡረታ የወጣች ሲሆን በለንደን ዩንቨርሲቲ የአፍሪካ የጥናት ትምህርት ቤት የአፍሪካ የጥናት ማዕከል የምርምር ተባባሪ ሆና እየሰራች ነው፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያና በብራዚል ካሉ ዩንቨርስቲዎች ጋር ለምርምርና ለማስተማር ግንኙነት እያጎለበተች ትገኛለች፡፡ የእሷ የምርምር ፍላጎቶችና የህትመቶቿ ርዕሶች የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ስነ-ጥበብና አርኪኦሎጂ ፣ የዲያስፖራ ጥናቶችና በተለይም ከግጭትና ውክልና ጋር የተያያዙ ፍልስፍናን እና ስነ-ጥበብን ያካተቱ ናቸው፡፡ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ በርካታ የምርምር ጉብኝቶችን አድርጋለች፡፡


መጀመርያ ትኩረቷ በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት የመካከለኛው ዘመን የግድግዳ ስዕሎች ላይ ነበር፡፡ ለዚህም ታሪካዊ፣ ስነ-ጥበባዊ ታሪክና፣ ኢትኖሎጂካል (የሰው ልጅ ባህሎችን የሚያጠና ዘርፍ) /ስነ-ሰብአዊ ገጽታቸውን ለመመልከት ዘርፈ ብዙ የጥናት መስኮችን በስራ ላይ አውላለች፡፡ 


እነዚህን መዳረሻዎችን በአርኪኦሎጂ ያዊ ሁኔታ ለማጥናት ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ የአሁኑን የሰለሞናዊና የዛጔ ነገስታት ግንኙነት የጥናት ቡድን እየመራች ትገኛለች፡፡ ዶ/ር ታንያ ትራይብ ለምርምር ስራዋ ብዙ ድጋፎችን አግኝታለች፡፡   

የቡድኑ አባላት

አማካሪዎች

ዶ/ር ዓለምሰገድ በልዳዶስ፡- የአካባቢ አርኪኦሎጂ ተመራማሪ (Environmental Archaeologist). ከአርኪኦሎጂና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፤ ኢትዮጵያ፡፡


ዶ/ር ዳሪኦ ፒኦምቢኖ ማስካሊ፡- ሳይፈርስ በሚቆይ አስከሬን ልዩ ባለሙያ ከቪለኒየስ ዩንቨርሲቲ፣ ሊቱንያ፡፡

 

ዶ/ር ፓትሪክ ኩኢን፡- በአርኪኦሎጂ ተቋም የአለት ተመራማሪ (Petrographer) ከለንደን ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ዩናይትድ ኪንግዶም፡፡


አቶ ስቴፈን ሪከርበይ እና ወ/ሮ ሊሳ ሸከደ፡- ተንከባካቢዎች ከለንደን ዩናይትድ ኪንግዶም እና ከኢትዮጵያ ቅርስ ደጋፊ አማካሪዎች


አቶ ጥላሁን ገብረስላሴ፡- የአለም ቅርሶች ምዝገባ ጥናት ከፍተኛ ተመራማሪ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ፣ ኢትዮጵያ፡፡ 

የቀድሞ የፕሮጀክቱ አባሎች (በወቅቱ የነበራቸው ግንኙነት)

    አቶ አበበ መንግስቱ፡- የመስክ አርኪኦሎጂ ባመለሙያ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ አዲስ አበባ፡፡


    ዶ/ር ማርክ አንደርሰን፡- የግል(በራሱ) የአርኪኦሎጂ ተመራማሪ፣ ዩናይትድ ኪንግዶም፡፡


    አቶ ቻላቸው ስሜነህ፡- የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ባህርዳር፡፡


    አቶ(አሁን ላይ ዶ/ር) ብራየን ክላርክ፡- የድህረ ምረቃ ተማሪ ሪሲ ዩንቨርሲቲ፣ ሆስተን አሜሪካ፡፡ 


    አቶ ሐብታሙ ተስፋዩ፡- የመስክ አርኪኦሎጂ ባለሙያ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ፣ አዲስ አበባ፡፡


    አቶ ኪዳነማርያም ወልደጊዮርጊስ፡- ላሊበላ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት፣ ላሊበላ፡፡


    አቶ ሉካ ሳቬሊ፡- በአፍሪካ የጥናት ትምህርት ቤት የድህረ ምረቃ ጽ/ቤት፣ ዩናይትድ ኪንግደም፡፡


    አቶ ዲል ሲንግህ ባሳንቲ፡- የድህረ ምረቃ ተማሪ ሰሜን ምዕራብ ዩንቨርሲቲ፣ ኢፋንሰቶን አሜሪካ፡፡


    ወ/ሮ ሞርገን ኤለይን ስሚት- የግል(በራሷ) የጨርቃ ጨርቅ ባለሙያ፣ ካናዳ፡፡ 

 

bottom of page