top of page

የመስክ አርኪኦሎጂ

እጅግ ብዙ ቅርሶች ያሉባቸውን አካባቢዎች ለመፈለግ በማሰብ የመስክ ስራ በሁሉም መዳረሻዎች ተካሂዷል፡፡ ይህ በይበልጥ የተስፋፋው ብራየን ክላርክ በገነተ ማርያም አካባቢ ሰፋ ያለ ቦታ ላይ ጥልቀት ከሌለው አንስተኛ መሬት ላይ ከ0.50 ሜትር ወይም ከዚያ በታች በሆነ ቁፋሮ ላይ ስራ የሰራ ቢሆንም በሽርሸራና በእርሻ ምክንያት አፈሩ ጥልቀት የሌለውና የንብብር እጥረት የነበረበት ነበር፡፡


በ2005 ዓ.ም በገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን የውጨኛ ግቢ (መድረኩ) ላይ ቁጥጥር የነበረበት አጭር ጊዜ የወሰደ ቁፋሮ አካሂደናል፡፡ በሽርሸራ ተቆርጦ የመከላከያ ግንብ ሊገነባለት በዝግጅት ላይ ከነበረው ኮረብታ ላይ የሰው አጥንቶች ተግኝተዋል፡፡ በጊዜ እጥረት ምክንያት በጣም ተጋላጭ በሆኑ በሶስት 1×1 ሜትር የሙከራ ጉድጓዶች ላይ ትኩረት ለማድረግ የወሰን ሲሆን የተገኙት አጽሞችም በለንደን የሙዚየም አርኪኦሎጂና በእንግሊዝ የቅርስ መመርያ መሰረት ተመዝግበው ተነስተዋል፡፡ 


በ2007 ዓ.ም በዚህ አዲስ በተገኘው የመቃብር ስፍራ ላይ ተጨማሪ ሥራ አካሂደናል፡፡ አካባቢውን በጥልቀት ዳሰሳ ጥናት ስናደርግና የክስተቶቹን ቅደም ተከተል ስናስቀምጥ በመረጋገጥ እየተጎዱ የነበሩ ቁጥራቸው ያልታወቀ ቀብሮች ተለይተዋል፡፡ አንድ የህንጻው ግድግዳ ላይ በነበረና በአራት ቀብሮች ላይ በጥንቃቄ ቁፋሮ የተደረገ ቢሆንም ውጣውረድ በበዛበት የመንግስት አሰራር ምክንያት ስራው ተደናቅፏል፡፡


በ2009 ዓ.ም በውስጠኛው የቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በሚገኙ ቀብሮች ላይ ስራ የጀመርን ቢሆንም ቁፋሮ እንደጀመርን ስራውን እንድናቋርጥና ቀብሮቹን እንደገና እንድንሞላ ተገደናል፡፡ በዚህ ምክንያትም የታቀደው ስራ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡
ከረዥም ጊዜ ደርድር በኋላ ቡድኑ በ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ውስጥ የሚቀጥለውን የመስክ ስራ ለማቀድ በ2012 ዓ.ም ጥር ወር ወደ ገነተ ማርያም እንደገና መጥቶ ነበር፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የኮሮና (COVID-19) ወረርሽኝ በዚህ አመት ተጨማሪ የመስክ ስራ እንዳይሰራ ከልክሏል፡፡ ለመስራት ምቹ በሚሆንበት ጊዜ ወዲያውኑ ስራችንን ለመጀመር እቅድ ያለን ሲሆን በ2013 ዓ.ም እንደሚሆን ተስፋ አለን፡፡

bottom of page