top of page

ገነተ ማርያም

የገነተ ማርያም መንደር በላስታ ወረዳ ውስጥ ከላሊበላ ከተማ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ የአየር ላይ ልኬት 11 ኪ.ሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኘው ከትልቁ ተከዜ ወንዝ በላይኛው ክፍል እና በአቡነ ዮሴፍ ተራራ (4260 ሜትር) መካከል ከባህር ወለል በላይ 2300 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ 

ቤተክርስቲያኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲሆን ለገዳማውያኖችና ለመንደሩ ነዋሪዎች ሃይማኖታዊ ግልጋሎት ይሰጣል፡፡ ይህ ቤተክርስቲያን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወይም በዚያ አካባቢ ከአለት (ከእሳተ ገሞራ ቁስ) ተፈልፍሎ የተሰራ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ በወፍራም ምሰሶና ቤተክርስቲያኑ በተፈለፈለበት ግድግዳ የውስጠኛ ጠባብ ግቢ የተከበበ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በደቡብ አቅጣጫ ባለው አጭር ዋሻ በኩል ነው፡፡ በ2007 ዓ.ም የድሮውን የቤተክርስቲያኑን መጠለያ በማስወገድና አዲሱን በመትክል መካከል በነበረው ጊዜ የቤተክርሰቲያኑን የጣርያ ላይ ጌጥ ያለ አንዳች እንቅፋት ሊታይ የቻለበት አጭር ጊዜ ነበር፡፡ በስተደቡብ አቅጣጫ ባለው የቤተክርስቲያኑ ፊትለፊት ምእመናን ለሃይማኖት ግልጋሎት የሚጠቀሙበት ‘መድረክ’ አለ፡፡ ቦታው ላይ ለመድረስ ከመንደሮቹ ጀምሮ የአቀበት መንገድን መውጣት ይጠይቃል፡፡ ከመድረኩ ፊት ለፊት ለእቃ ማስቀመጫ፣ ለሙዚየምና ለመነኩሳት መኖርያ ታስበው በቅርብ የተሰሩ ሁለት ህንጻዎች አሉ፡፡ እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ እነዚህ ቤቶች ባህላዊ ክብ ቱኩሉዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን አሁን ብዙዎቹ በብዙ ዘመዊ ቁሳቁሶች እንደገና ተገንብተዋል፡፡ ገነተ ማርያም ለምርምር/ለጥናት ስራ ቅርብ ሆኖ የተመረጠበት ምክንያት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ያሉት ስዕሎችና የሰሎሞን ስርወ-መንግስት የመጀመርያ መሪ የሆነውን ንጉስ ይኩኖ አምላክ ምስል ‘በእግዚአብሔር ምስጋና፤ እግዚአብሔር በፍቃዱ ያነገሰኝ እኔ ንጉስ ይኩኖ አምላክ ቤተክርስቲያን አነጽኩ፡፡’ የሚል ጽሁፍ ያካተተ መሆኑ ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው ቦታው የሰለሞን ስርወ-መንግስት ጎራዎች በሚስፋፉበት ወቅት አስፈላጊ/ጠቃሚ መዳረሻ እንደነበረ ነው፡፡

 

bottom of page