top of page

ዋሻ ሚካኤል

የዋድላ አምባ ከተከዜ ሸለቆ ደቡባዊ አቅጣጫ በጉልህ ከፍ ብሎ ከባህር ጠለል ከ3000 ሜትር በላይ ከፍታ የሚገኝና በደቡብ ጥልቅ በሆነው የዥጣ ወንዝ ገደላማ ሸለቆ የሚዋሰን ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ከላሊበላ ከተማ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በአየር ላይ ለኬት 37 ኪ.ሜ ወይም በመንገድ ላይ ልኬት 94 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በዝቅተኛ ኮረብታዎች በተከበበው ሰፊ ሸለቆ መካከል ያገጠጠ ድንጋይ ካለበት አለት የውስጠኛ ክፍል ይገኛል፡፡ 


ምን አልባት በሰው ሰራሽ የሰፋ ተፈጥሯዊ ዋሻን የያዘ ሲሆን መግቢያው በግንብ ታጥሯል፡፡ የቤተክርስቲያኑን የውስጠኛ ግድግዳ ያስጌጡት ስዕሎች አሳሳል ዘይቤ/ዘዴ ገነተ ማርያም ከተገኙት ስዕሎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡. ከነዚህም በዝቅተኛ እፎይታ የተቀረጹ ረዥም በቅብ ያጌጡ የአደንና የእረኝነት ትዕይንቶች ናቸው፡፡


በሸለቆው ዙሪያ ባሉ ቋጥኞች ውስጥ በቤተክርስቲያኑ መውጫ፣ ጀርባ እና ጎኖች ውስጥ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ትናንሽ ዋሻዎች ይገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ የሰው ቅሪት አካላትን የያዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን የተወሰኑት ለአካባቢው ማህበረሰብ ለመኖርያ ቤትና ለእቃ ማከማቻ በመሆን እስካሁን ድረስ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከቤተክርስቲያኑ በስተሰሜን በኩል 600 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኝ ኮረብታ ላይ የአንድ ቤት መሰረት (ውሃ ልክ) ሆኖ  የሚታይ መዋቅር ያለ ሲሆን እንደ አካባቢው ወግ ከሆነ የንጉስ ይኩኖ አምላክ አያት የመሃሪው አምላክ ቤተ-መንግስት እነደሆነ ይነገራል፡፡


ከዥጣ ሸለቆ ወጣ ብሎ ከአምባው ወልል በታች 650 ሜትርና ከሸለቆው ወለል በላይ 170 ሜትር ደቡብ አቅጣጫ በግምት ከዋሻ ሚካኤል ቤተክርስቲያን 3 ኪ.ሜ ላይ ሜሎጥ አምባ ተብሎ የሚጠራ የድንጋይ ጉብታ አለ፡፡ ከአምባው ወደ ሜሎጥ አምባ በአንድ ብቸኛ ገደላማ መንገድ የሚደረስ ሲሆን ይህም ይኩኖ አምላክ ንጉስ ከመሆኑ በፊት ለተወሰነ ጊዜ የታሰረበት ‘እስርቤት’ ነበር ተብሎ ይታመናል፡፡

bottom of page