top of page

የእንስሳት አርኪኦሎጂ

የእንስሳት ቅሪተ አካላት

በገነተ ማርያም ዙርያ ከሚገኘው የእርሻ መሬት ላይ በጥቂት መቶዎች የሚቆጠሩ ቁርጥራጭ የእንስሳት አጥንትና ጥርስ የተሰበሰበ ሲሆን አብዛኛዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰባበሩ ናቸው፡፡ አጥንቶቹ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች አሁንም ድረስ ተጠብቀው ያሉ የቤት እንስሳትን ማለትም ዶሮዎችን፣ በጎች/ፍየሎችንና ከብቶችን ይወክላሉ፡፡


ከሶስቱ እንስሳቶች መካከል የተወሰኑት ለምግብነት እንደዋሉ ይጠቁማሉ፡፡ ከነዚህ የቤት ውስጥ ዝርያዎች ጋር የማይጣጣሙ ጥቂት አጥንቶች ደግሞ ረጅም የፊት ጥርስ ያላቸውን አይጦች የሚወክሉ ሲሆን (ምን አልባት ለጋራ ጥቅም በማሰብ ግንኙነትን የፈጠሩ እንስሳት)፣ የአእዋፍ ዝርያዎች ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ጅግራ ያሉ እና ምን አልባትም ያልታወቁ ትንንሽ አጥቢ እንስሳት ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡


ምንም እንኳ የዶሮ፣ የበግና የፍየል አጥንት ቁርጥራጭ ከከብቶች የአጥንት ቁርጥራጭ እጅግ እንደሚበልጡ ግልጽ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የተገኙት አጥንቶች የተሰባበረ ባህሪይ/ተፈጥሮ የዝርያዎቹን ጾታ፣ እድሜ፣ ሁኔታና ሂደት ላይ በመረጃ የተደገፈ ትንታኔ እንዳይደረግ ከልክሏል፡፡


በገነተ ማርያም በሚገኘው መቃብር ስፍራ ላይ በተደረገ ቁፋሮ ወይም በሌሎች የፕሮጀክቱ ቦታዎች ላይ በተደረገ የመስክ የእግር ጉዞ ወቅት እስካሁን ድረስ ምንም የእንስሳት ቅሪት አልተገኘም፡፡

እንስሳት በኪነ-ጥበብ ውስጥ

በብዙ የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ውስጥ እንስሳት በግድግዳ ስዕሎች ላይ ይታያሉ፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ እየተጠኑ ያሉ መዳረሻዎችም ከነዚህ አብያተ ክርስቲያናት የተለዩ አይደሉም፡፡ የዱር እንስሳትና የቤት ውስጥ እንስሳቶች ለብቻቸው ወይም ከተወሰኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ አፈ ታሪኮች፣ ታሪካዊ የሃይማኖት ሰዎች ለሃይማኖታቸውና አንዳንድ ጊዜም ለፖለቲካዊ ጠቀሜታቸው በአንድ ላይ ሆነው ይታያሉ፡፡ በዋሻ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዙርያ በግድግዳ ላይ የተቀረጹ (low-relief ) በቅብ ያጌጡ መስመሮች የአደንና የእረኝነትን ትዕይንቶችን የያዙ ናቸው፡፡ እዚሁ ቦታ የዱር እና የቤት እንሰሳትን ከሰው ምስሎች/ቅርጾች ጋር ተዛምደው እንመለከታለን፡፡ ነገር ግን የእነሱ ጠቀሜታ ያን ያህል ግልጽ አይደለም እንዲሁም ሁልጊዜ በቀላሉ የሚታወቁ አይደሉም፡፡ የተወከሉት የዱር እንስሳት እንደ ዝሆንና ቀጭኔ ያሉ ዝርያዎችን ያካተተ ሲሆን  እዚህ ከባህር ወለል ከ3000 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው ገደላማ የዋድላ ከፍተኛ ቦታ ላይ እነዚህ እንስሳቶች በጭራሽ ላይከሰቱ ይችል ይሆናል፡፡ 

bottom of page