top of page

የሰው አፅም አርኪኦሎጂ

የኦስቲዮ አርኪኦሎጂ / ሂውማን ባዮአርኪኦሎጂ ጥናት ስለ ግለሰቦችና ህዝቦች መረጃ መልሶ ለማግኘት ሲባል የሰዎችን ቅሪተ አካል የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ ስለ አኗኗቸው፣ ስለ ጤንነታቸው ሁኔታ፣ ከሌሎች ሰዎችና ከአካበቢው ጋር ስላላቸው ግንኙነት፣ ስለ ማህበራዊ ሥነ-ስርአት ልምዶቻቸውና ስለ ሞታቸው ሊነግረን ይችላል፡፡ 


እስካሁን ድረስ በፕሮጀክቱ የተከናወነው የሰው ቅሪተ አካል ጥናት በገነተ ማርያም ከሚገኘው የመቃብር ስፍራ በቁፋሮ የተገኘውን አነስተኛ ቡድን ያላቸው ግለሰቦችና ጥቂት የተሰባበሩ የሰው ልጅ ቅሪቶችን አካቷል፡፡ የናሙናው የራዲዮ ካርቦን ውጤት እንደሚጠቁመው የመቃብሮቹ እድሜ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ወይም ከዚያ በኋለ የነበሩ እንደሆነ ያሳያል፡፡


በሁለቱም ጾታዎች ከሞት የእድሜ መጠናቸው ጋር ተወክለዋል፡፡ እናም ብዙ ቁጥር ያላቸው የስነ-ህመምና አሰቃቂ ሁኔታዎች እንደነበሩባቸው መረጃዎች ነበሩ፡፡

 

  • ጥርስን እንደ መሳርያነት መጠቀም ለጥርስ በሽታ እንዳጋለጣቸው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

  • የአጥንት እብጠትና መንፈሰ ልል የመሆን በሽታ (Osteoarthritis/Degenerative disease) በእርጅና ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ግን ደግሞ ከከባድ የአካል እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይችላል፡፡ 

  • የአንቲ-ሞርተም አጥንት ስብራቶች (በግለሰቦች ህይወት ወቅት የተከሰቱ ናቸው) ከአስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥ ጋር መታገል የተቆራኘ ሊሆን ይችላል፡፡

  • የአጥንት መጣመም በሽታ(የቫይታሚን ዲ እጥረት)፡፡ የአመጋገብ ችግርና የፀሐይ ብርሃን የማግኘት ችግር ውጤት ነው፡፡


በተጨማሪም የጉዳት ምክንያት ሊሆኑ በሚችሉ የዱር ንቦች ወይም ተርቦችና በአይጠመጎጥ መቆረጣጠም መልክ የታፎኖሚክ/ taphonomic (ህይወት ያላቸው አካላት እንዴት እንደሚበሰብሱና ወደ ቅሪተ አካል እንደሚለወጡ የሚያጠና) ለውጥ መረጃዎች ነበሩ፡፡


ለቀጣይ ጊዜ የታቀደው ስራ የተሰባበሩና የተደበላለቁ ቅሪቶችን(ባሉበት አካባቢ የተገለጹ) መመዝገብ፣ መሰብሰብ፣ መመርመር እና ከዋሻ ውስጥ ቀብሮች ማለትም ዋሻ ሚካኤልና ይምርሓነ ክርስቶስ ውስጥ ተከማችተው ከሚገኙት አጽሞች ጋር ማነጻጸርን ያካተተ ነው፡፡ ለራዲዮካርቦን ምርመራ ተጨማሪ ናሙናዎችን እንልካለን፡፡
 

bottom of page