top of page

ብልባላ ቂርቆስ

ይህ ከአለት የተፈለፈለ ቤተክርስቲያን ከላሊበላ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው መንገድ ትንሽ ራቅ ብሎ ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኑ ከአለት የተፈለፈለ ሲሆን በቤተክርስቲያኑና በቀሪው አለት መካከል በሚገኘው ጠባብ ቦይ የተከበበ ነው፡፡  


ኪነ-ህንጻው በብዙ መንገድ ከገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር ይመሳሰላል፡፡ የኪነ-ህንጻው መመሳሰል በውስጠኛው የቤተክርስያኑ ክፍል የቀጠለ ሲሆን በግርግዳው ላይ ተሸፍነው የሚታዩት ቀዳሚ/ዋና ስዕሎች ምንም እንኳ እይታቸው የጠፉ ቢሆንም ገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚገኙት ስዕሎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያኑ በልዩ ልዩ የዛፍ አይነቶች የተከበበ ሲሆን በእነርሱ ስር የአካባቢው ማህበረሰብ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን ያደርጋል፡፡

bottom of page