top of page

እመኪና መድኃኔ ዓለም

ይህ ቤተክርስቲያን ከአቡነ ዮሴፍ ተራራ እሰከ ላይኛው የገነተ ማርያም ክፍል በሚዘልቀው የእመኪና መድሃኒዓለም የተራራ ጠርዝ አጠገብ ከባህር ወለል በላይ 3000 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኝ ትልቅ ዋሻ ውስጥ የተገነባ ነው፡፡

  ከገነተ ማርያም ለሶስት ሰዓታት ተራራው ከተወጣ በኋላ በእግር ጉዞ ብቻ ቦታው ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ከአክሱማውያን ዘመን በኋላ የተሰራ የኪነ-ህንጻ ዘዴ ሲሆን በይዘቱ ትንሽ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ምንም እንኳ የተለመደው የንብብር ኬክ ገጽታ ቢኖረውም (የይምርሓነ ክርስቶስን ቤተክርስትያን ይመልክቱ) ከእንጨትና ከድንጋይ ግንብ ይልቅ ቀይ ኖራና በግራጫ ሸክላ ስብርባሪ ተለዋዋጭ ንብብሮች የተሰራ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑ የጣራው ጉልላትና ኩርቻ ቅርጾች ከይምርሓነ ክርስቶስ ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የቤተክርስቲያኑን የውስጠኛ ግድግዳና ጣራ ያስጌጡት ስዕሎች በአሳሳል ዘይቤያቸው ከገነተ ማርያም ስዕሎች ጋር ይመሳሰላሉ፡፡

bottom of page