top of page

ሸክላዎችና ሌሎች ትንንሽ ግኝቶች

በገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ጥልቀት ከሌለው አነስተኛ መሬት 0.50 ሜትር ወይም ከዚያ በታች በሆነ የሙከራ ቁፋሮ እንዲሁም በአርሶ አደሮች ማሳ ገጸ ምድር አቀበታዊ ተዳፋት ላይ ብራየን ክላርክ የሸክላ ስብርባሪዎችን አግኝቷል፡፡ ቢሆንም በተሸረሸረ አፈር ውስጥ በአፈር ንብብር /stratigraphy/ ማጣት ምክንያት ውጤታማ በሆነ መልኩ እድሜውን ማወቅ አልተቻለም፡፡ ከቀብር ጉድጓዶች የተገኙ የተወሰኑ ቁሶች ከተቀበሩት የሰው አጽሞች ወይም ቁሶች ጋር አይዛመዱም ነበር፡፡ ነገር ግን ለቀብሩ መሸፈኛ/መሙያ ከነበረው አፈር ጋር ይዛመዳሉ፡፡


የተገኙት አብዛኛዎቹ ሸክላዎች ትናንሽ፣ ወፍራም ‘የተጠቀለሉ’ በአብዛኛው ያልተጌጡ ነበሩ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቹ ጠቃሚ ‘የምርምር’ ባህሪይ (የክብ ነገር ጠርዝ፣ እጀታ፣ መቀመጫና ጌጣጌጥ) የነበራቸው ናቸው፡፡ እስካሁን ሙሉ የሆነ የወጥ መክደኛ ተገኝቷል፡፡ ስለ አርኪኦሎጂ ግኝቶች ጥልቅ የሆነ ምርመራ ለማቅረብና ቀደም ሲል የነበረውን አገልግሎታቸውንና ስለ ድስቶቹ ስያሜ፣ ባህሪያቸውና ለአከባቢው ማህበረሰብ የሚሰጡትን ጥቅም ለማወቅ ከአካባቢው ሸክላ ሰሪዎች ጋር የኢትኖግራፊክ (ተመራማሪዎች ስለ አንድ የተወሰነ አሰራር የበለጠ ለማወቅ እድሎችን እንዲያገኙ ይረዳቸዋል) ቃለ መጠይቅ ተደርጓል፡፡


በፔትሮግራፊክ ትንታኔ የአንዳንድ የሸክላ ስራዎች ትንታኔ በፓትሪክ ኩይን (የለንደን ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ) ተከናውኗል፡፡ በዚህም ከሸክላ ጋር የተደባለቁ ቁሳቁሶችንና አለቶችን ለይቶ አውቋል፡፡ የጂኦሎጂካል ካርታዎች እንደሚያመለክቱት እቃዎቹ በአመዛኙ በገነተ ማርያም አካባቢ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ይህም የወጥ ቤት እቃወቹ (ድስቶቹ) በአገር ውስጥ እንደተመረቱ ይጠቁማሉ፡፡ 


አንዳንድ የሸክላ ስራዎች በሌላ ቦታ ከሚገኙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማለትም በአክሱምና በጣና ሀይቅ አካባቢ ከተገኙ የወጥ ቤት እቃዎች (ድስቶች) ጋር ተነጻጻሪ ናቸው፡፡


ከሸክላዎች በተጨማሪም ባልጩት (ከእሳተ ገሞራ የሚሰራ ጥቁር የመስታውት ድንጋይ) ቢለዋዎችንና የብረታ ብረት ስራን ጨምሮ አንዳንድ የድንጋይ ቅርሶች በሁለቱም በገነተ ማርያምና በዋሻ ሚካኤል ተገኝተዋል፡፡

bottom of page